Episode Description
"የበርሊን መውደቅ አውሮፓውያን የበላይ እንዳልሆኑና አፍሪካን ለመግዛት እንዳልተፈጠሩ ያስተማረ ታሪካዊ ክስተት ነው" ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ፕሮግራማችን ሁለት ዋና ዋና አህጉራዊ ጉዳዮችን እንቃኛለን፦ በክፍል 1 የናዚ ፋሺዝም መሸነፍ ግንቦት 1 / May 9 እና የሶቪየት ህብረት የከፈለችው መስዋዕትነት የኮሎኒያሊዝምን የሐሰት ትርክት እንዴት እንዳፈረሰው፤ ይህም ለዛሬው የሩሲያ-አፍሪካ የጋራ ሉዓላዊነትና የጸረ ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ንቅናቄ እንዴት መሰረት እንደሆነ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ጋር ያደረግነውን ውይይት እናቀርባለን። በክፍል 2 መሠረተ-ልማት ከጥሬ ዕቃ ማጋዣነት ወጥቶ የራሱን ሕዝብ ወደሚያገለግል የውስጥ እሴት ማደጉን፤ እንደ ሊቲየም እና ኮባልት ያሉ ወሳኝ ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ምንዛሬዎች በመገበያየት "ዘመናዊነት ማለት ምዕራባዊነት እንዳልሆነ" የዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና የንግድ ትስስር ከፍተኛ አማካሪ ጉንተር ባይሰል ጋር የዳሰስነውን ይዘን ቀርበናል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ፦