የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አድልዖ እና የአፍሪካ መዋቅራዊ ሉዓላዊነት ግስጋሴ

May 21
1 hr

Episode Description

''ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ነጻነቱን በአግባቡ አውጆ ለፍትህ የተቋቋመ ሳይሆን ለምዕራባውያኑ ብቻ የሚያገለግል የምዕራባውያን ተቋም ሆኗል። በመሆኑም ታማኝነቱን ካጣ የፖለቲካ መሣሪያ ጋር አፍሪካውያን አብረው ሊቀጥሉ የሚችሉበት ምንም ምክንያት የለም'' ሲሉ የሕግ ባለሙያው አቶ ዳንኤል ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

 በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት በክፍል 1 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኢራን ንጹሃን ተማሪዎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ዝምታን መምረጡ የተቋሙን አድሏዊነት እንዴት እንደሚያጋልጥ ከሕግ ባለሙያው ዳንኤል ፍቃዱ ጋር ያደረግነው ቆይታ ይዘናል፡፡ በክፍል 2 የኢትዮጵያ የብሪክስ የአዲሱ ልማት ባንክ አእና መሰል አማራጭች የሚሰጠው ስልታዊ ፋይዳ በተመለከተ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር ያየው ገነት ጋር ተወያይተናል፡፡ በክፍል 3 ኢትዮጵያ የምዕራባውያንን “መርምሮ ማረድ” ሴራ በመስበር፣ የእንስሳት ሀብቷን ለመታደግ “መርምሮ መለየት” የተሰኘውን አዲስ ሀገር በቀል አሰራር ይፋ ማድረጓን በተመለከተ ፤ ከኢትዮጵያ እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማቲዎስ ላቀው ጋር የተደረገ ልዩ ቆይታእናቀርባለን።

 ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:


See all episodes