View Transcript
Episode Description
''አፍሪካ የአየር ክልሏን፣ የንግድ ፍሰቷን እና የመንገደኞች እንቅስቃሴን በራሷ እጅ በማስገባት መዋቅራዊ ሉዓላዊነቷን ማረጋገጥ አለባት'' ሲሉ የአቪዬሽን ተንታኝ ደሪክ ንሴኮ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ እ.ኤ.አ ከሰኔ 15 አእስከ ሰኔ 19 ፣ 2026 በቶጎ ሌሜ የሚካሄደው የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ኮንቬንሽን እና ኤክስፖ ለአህጉሪቱ የተዋሃደ የአየር ክልል (SAATM) መፈጠር ምን ዓይነት ተግባራዊ ዕድሎችን ይዞ ይመጣል? የአየር ትኬት ዋጋንና ቀረጥን በመቀነስ ረገድስ ምን ሚና አለው? ስንል ከአቪዬሽን ተንታኝ እና የኤር ስፔስ አፍሪካ መስራች ደሪክ ንሴኮ ጋር ሰፊ ቆይታን አድርገናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የአፍሪካን የውሃ ሀብትና ስነ-ምህዳር ከኬሚካል ብክለት ለመጠበቅ የምዕራባውያንን የተጽዕኖ ሞዴሎች በመተው፣ የደቡብ-ለደቡብ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምርምር ትብብሮች ለአህጉሪቱ ሉዓላዊነት ስላላቸው ወሳኝ ጠቀሜታ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ቶክሲኮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሰብለወርቅ መኮንን ሸገን ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡