View Transcript
Episode Description
''ሩሲያ በአፍሪካ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ከተለመደው የዕርዳታ ወጥመድ ወጥቶ የረጅም ጊዜ አህጉራዊ ምርታማነትን፣ የኢነርጂ ዋስትናን እና እውነተኛ የኢኮኖሚ ነፃነትን የሚገነባ አወንታዊ የልማት አጋርነት ነው'' ሲሉ አሜሪካዊት የቢዝነስ ስራ ፈጣሪ እና በአፍሪካ ከአስር አመታት በላይ ተግባራዊ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ ልምዳቸውን እያካፈሉ የሚገኙት የሪፕልናሚ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄይ ኮኖሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በአዲሱ ባለብዙ-ዋልታ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ሩሲያ በአፍሪካ የምታደርገው የመሠረተ-ልማትና የኢነርጂ ኢንቨስትመንት ከተለመደው የዕርዳታ ሞዴል በምን ይለያል? አህጉራዊ የመረጃ ሉዓላዊነትንና የኢ-ገቨርናንስ ሥርዓትን በመገንባት ረገድስ የቴክኖሎጂ ባለቤትነት ምን ዓይነት የፋይናንስ አቅምን ይፈጥራል? ስንል ከሪፕልናሚ ሊቀመንበርና ስራ አስፈፃሚ ጄይ ኮኖሊ ጋር ሰፊ ቆይታን አድርገናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የኢትዮጵያ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ ለአፍሪካ ሀገራት ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ ምን ዓይነት መዋቅራዊ ትምህርቶችን ሰጥቷል? የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት፣ የዲጂታል ምዝገባ ቴክኖሎጂ እና የ"መደመር" ፍልስፍና የምዕራባውያንን የአተራሪክና የማረጋገጫ የበላይነት ፍላጎት እንዴት መመከት እንደቻሉ ከፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና ነዋሪነታቸው አሜሪካ ከሆኑት የህግ ባለሙያ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡