View Transcript
Episode Description
''በምዕራባውያን ፈንድ ላይ ብቻ ተመስርቶ ሌሎችን ለማጥመድ የተቋቋመው የአይሲሲ (ICC) መዋቅር ወደፊት ይሻሻላል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም፤ በመሆኑም አፍሪካ በራሷ አቅም እና ቀጠናዊ ትስስር የፍትህ ስርዓቷን መገንባት አለባት'' ሲሉ የህግ ባለሙያው ዐምደገብርኤል አድማሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የቱርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የማሊ፣ ኒጄር እና ቡርኪናፋሶ ጥምረት ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውጣት የወሰኑትን ታሪካዊ እርምጃ መነሻ በማድረግ ከህግ ባለሙያው ዐምደገብርኤል አድማሱ ጋር ጋር በጥልቀት ተወያይተናል። አፍሪካውያን በተቋሙ መሻሻል ላይ ተስፋ በመቁረጥ ከምዕራባውያን የህግ ወጥመዶች ወጥተው፣ በገንዘብና በመዋቅር ራሱን የቻለ ቀጠናዊ የፍትህ ስርዓት ለመዘርጋት ስላላቸው አማራጭ የዲፕሎማሲ መንገዶች ተነጋግረናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡