·S1 E14
የማንዴላ ቀን፡- ከፀረ-ቅኝ ግዛት እስከ ብሪክስ ጥምረት የኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ አጋርነት በባለብዙ-ዋልታ ዓለም
View Transcript
Episode Description
''ኢትዮጵያ በፋሺስት ወረራ ወቅት በሊግ ኦፍ ኔሽን ተለይታና ተትታ በነበረችበት አስቸጋሪ ወቅት፣ የተጨቆኑ አገራት ሉዓላዊነታቸውን ለማስከበር በቅድሚያ እርስ በርስ መደጋገፍና የጋራ ጥምረት መፍጠር እንዳለባቸው የነፃነት አባቶቻችን ተረድተው ነበር፤ ዛሬም ቢሆን የአፍሪካ አገራት የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ከውጭ ጫና ነፃ ለመሆን ይህንን የማይደራደር የወንድማማችነት ትብብር በተግባር ሊያሳዩት ይገባል'' ሲሉ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ እና የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል፡፡
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት በየዓመቱ ሐምሌ 18 የሚታሰበውን የማንዴላ ቀንን መነሻ በማድረግ፣ የደቡብ አፍሪካው የነፃነት አባት ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ታሪካዊ ትስስር እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት አዲስ አህጉራዊ ጥምረት (በብሪክስ፣ በአፍሪካ ሕብረት እና በፀረ-ቅኝ ግዛት ታሪካቸው ላይ) ከልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ጋር በሰፊው እንወያያለን።
በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ የአፍሪካ ሀገራት በአዲሱ ባለብዙ-ዋልታ የዓለም ሥርዓት እና በብሪክስ መድረክ ላይ ያላቸውን ስልታዊ ተሳትፎ ከዛምቢያ የጥናትና ምርምር ማዕከል የምርምርና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ቺሳላ ብዋልያ ጋር እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡