የላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝት እና የኢኮኖሚና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂ

July 18
1 hr

View Transcript

Episode Description

''የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉዟቸውን በኢትዮጵያ ጀምረው በሳህል ቀጠና እና በሞዛምቢክ ማጠናቀቃቸው፤ ሞስኮ በባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት ላይ የተመሰረተ እውነተኛና ፍትሃዊ አጋርነትን ለመገንባት የምታደርገውን ሰፊ ስትራቴጂ በግልጽ ያሳያል'' ሲሉ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ምሁሩ ጥላሁን ሊበን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። 

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የላቭሮቭን የአፍሪካ ጉዞ መነሻ በማድረግ አህጉሪቱ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ እያካሄደች ያለችውን "ሁለተኛውን የነጻነት ማዕበል" እና የሩሲያ-አፍሪካ ስልታዊ አጋርነትን ከዲፕሎማሲ ምሁሩ ጥላሁን ሊበን ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ አፍሪካ ከምዕራባውያን ማዳበሪያና የላብራቶሪ ዘሮች ጥገኝነት ወጥታ፣ በሀገር በቀል እውቀትና ሳይንሳዊ ምርምሮች ታግዛ የራሷን የምግብ ሉዓላዊነት እና የጂኦ-ፖለቲካ ጥንካሬ የምታረጋግጥበትን ወሳኝ ስልቶች ከግብርና ኤክስቴንሽን ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዳንኤል ተመስገን ጋር በሰፊው ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡


See all episodes