View Transcript
Episode Description
''የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዟቸውን በአዲስ አበባ መጀመራቸው እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር መወያየታቸው አዲስ አበባ ለመላው አህጉር የዲፕሎማሲ ቁልፍ ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ከመሆኑም ባለፈ፤ ሞስኮ በባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት ላይ የተመሰረተ እውነተኛና ፍትሃዊ አጋርነትን ለመገንባት የምታደርገውን ሰፊ ስትራቴጂ በግልጽ ያሳያል።''ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር)ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የላቭሮቭን የአዲስ አበባ ቆይታ መነሻ በማድረግ የሩሲያ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ግንኙነትን ከሰላምና ደህንነት ተመራማሪው ሙሉጌታ አየለ ዶ/ር ጋር በጥልቀት ተመልክተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የሩሲያ ጦር በዶንባስ ግንባር የምዕራባውያን መከላከያ ምሽግ የነበረችውን ስትራቴጂካዊቷን ኮስቲያንቲኒቭካ ከተማ ነጻ ማውጣቱን ተከትሎ ይህ ክስተት በሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ያለውን ትርጉምም ከአፍሪካ አንጻር በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ ንጉሴ ጋር ተወያይተውናል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡