ከእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያነት እስከ ፍርደ ገምድልነት፦ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት መዋቅራዊ ቀውስ

June 2
1 hr

View Transcript

Episode Description

''የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) የዳኝነት ሥልጣን ዓለም አቀፋዊ አይደለም፤ ገለልተኛም አይደለም። ጠንካራ ግለሰቦችና የአፍሪካ መሪዎች የምዕራባውያንን ብሔራዊ ጥቅም ሲፈታተኑ የሮም ስምምነትን መዋቅራዊ ቀዳዳዎች በመጠቀም የማሸማቀቅና ገደብ የማበጀት እርምጃ ይወሰድባቸዋል'' ሲሉ የሕግ ምሁርና ተመራማሪ አቶ መታገስ ውለታው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

 በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በሮም ስምምነት የተመሠረተው ICC በአፍሪካና በግሎባል ሳውዝ ላይ ስላለው ተፅዕኖ በሰፊው ዳስሰናል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በአይሲሲ ላይ የሰነዘሩትን ብርቱ ትችት መነሻ በማድረግ፤ አፍሪካ የምዕራባውያንን የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ፖለቲካ ለመመከት እንደ ብሪክስ ያሉ አማራጭ ጥምረቶችንና አህጉራዊ የፍትሕ መዋቅሮችን እንዴት መጠቀም እንዳለባት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር መታገስ ውለታው ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፦

See all episodes