View Transcript
Episode Description
''ታሪካዊው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ፤ ለሀገራዊ ችግሮች ከምዕራባውያኑ የሚመጣን አንድን መፍትሄ ለሁሉም የሚል ‘one-size-fits-all approach’ በመተው፣ አገሪቱ ብቻ ሳትሆን መላው አፍሪካ እና የደቡቡ ንፍቀ ክበብ ያለ ውጭ ጣልቃገብነት የራሳቸውን ሰላም በራሳቸው እውቀትና ፍልስፍና መገንባት እንደሚችሉ በተግባር የሚያሳይ ታላቅ ማረጋገጫ ነው'' ሲሉ የፖሊሲ እና አስተዳደር ምሁሩ ጂሬኛ ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት የመጀመሪያው ክፍል ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የጀመረውን የኢትዮጵያ ታሪካዊ የምክክር መድረክ መነሻ አድርገን አፍሪካ ለችግሮቿ መሰል የምክክር መንገዶች ያላቸውን አቅም እንፈትሻለን፡፡ ለዚህም የፖሊሲ እና አስተዳደር ምሁሩ ጂሬኛ ታደሰን ጋብዘናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ሰው ሰራሽ አስተውሎት በኪነጥበብ ዘርፍ ለአፍሪካ የፈጠራ ባለሙያዎች እንዴት ረዳት ሊሆን ይችላል ስንል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ በተፈጥሮ የቋንቋ 'ፕሮሰሲንግ' ፣ ማሽን ለርነንግ' እና ዳታ ሳይንስ ተመራማሪ ወንድወሰን ሙሉጌታ (ዶ/ር)ን አነጋግረናል። በመጨረሻም የአካባቢ ጥበቃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ መረጃ-ተኮር እና በይነ-መረባዊ የካርታ ስራዎችን በመጠቀም የተፈጥሮ ሀብቶችን እና የዱር እንስሳቶችን ከጥፋት ለመታደግ የሚደረጉ ጥረቶችን በተመለከተ የብዝሃሕይወት እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ተመራማሪ ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር) በስፋት ተመልክተነዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ