Episode Description
"ወጣቶቻችን እውነተኛ ማንነታቸውን አውቀው እንዲታጠቁ ካደረግን ከ10 እና 20 ዓመታት በኋላ የሚጠፉ አይሆኑም፤ ይልቁንም በባህላቸው እየኮሩ ለዓለም የሚያስተዋውቁ እነሱ ይሆናሉ።" ሲሉ በጋና የባህላዊ መሪ፣ የ'ቴስት ኦፍ አፍሪካ' ተባባሪ መስራች እና የ'ሲስተር ኪንግደም ኔትወርክ' መስራች የሆኑት ቴንጎል ክፕሌማኒ ለስፕትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፤ አፍሪካ ከመደበኛው የመንግስት መዋቅር ባለፈ በጥንታውያን መንግስታቷ እና በባህላዊ እሴቶቿ አማካኝነት ያላትን የአንድነት አቅም እንቃኛለን። በጋና የባህላዊ መሪ፣ የ'ቴስት ኦፍ አፍሪካ' ተባባሪ መስራች እና የ'ሲስተር ኪንግደም ኔትወርክ' መስራች ከሆኑት ከቴንጎል ክፕሌማኒ ጋር በመሆንም፤ የቅኝ ግዛት ድንበሮች ያሻከሩትን የታሪካዊ ትስስር ዳግም ማጠናከር ስለሚቻልባቸው መንገዶች፣ የባህላዊ ተቋማት ለዘመናዊ አስተዳደርና ለኢኮኖሚ ትብብር ያላቸውን ፋይዳ፣ እንዲሁም ባህላዊ ማንነትን ለሰላምና ለቱሪዝም ልማት ስለመጠቀም በዝርዝር እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦