የዓድዋ ድል፦ የኢትዮጵያዊያንን የትብብር አቅም የገለጠ የአፍሪካዊያን ኩራት

March 2
1 hr

Episode Description

ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ክብርና ችሎታ ምልክት ሆኗል።[...]ፓን አፍሪካኒስቶች ማንሰራራት የቻሉት የ1896 እ.ኤ.አ የአድዋ ድልን ተከትሎ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያን እንደ ማረጋገጫ ወስደው፣ አፍሪካውያን የአውሮፓን የበላይነትና ቅኝ ግዛት መቋቋም እንደሚችሉ ተመልክተዋል። ሲሉ በወሎ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ባልቻ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ለ130ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የዓድዋ ድል በዓል መነሻ አድርገን ሉዓላዊነትን በሶስት መልኩ ቃኝተነዋል። በቀዳሚነት ኢትዮጵያ በዓድዋ የተቀዳጀችውን ድል መነሻ አድርገን ለአፍሪካ ስላለው ትርጓሜ በወሎ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ባልቻ ጋር በሰፊው ዳስሰናል። በሁለተኝዉ ክፍል የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መገለጫ ስለሆነዉ ቋንቋና ሉዓላዊነትም የሚዲያ ባለሙያ እና የድምፅ ተዋናይ ኮስሞ ሚለር ጋር በሁለተኛው ክፍል ቆይታ አድርገናል። በመጨረሻም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረታችንን አድርገን ከ'ኤአይ' የሚሰጠንን መረጃ ማን ይወስናል ስንል ስንል ለ21ኛው መቶ ክፍለዘመን የአፍሪካ የትርክት መልክ አማራጭ ሀሳቦችን ከዲጂታል አስተዳደርና ትራንስፎርሜሽን ባለሙያው እስክንድር ቸርነት ጋር ፈትሸናልን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.