Episode Description
"[ኢትዮጵያ] በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር እንደመሆኗ፣ በአንድ [በጅቡቲ] ወደብ ላይ ጥገኛ መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ አሁን ፍላጎታችንና ጥቅማችን በጣም የተለያየ ነው። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ወደቦችን መጠቀም፣ መመልከት ወይም ��ፈለግ እጅግ አስፈላጊ ነው።" ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር የሆኑት አቶ በላይ በየነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በርበራን ከጎበኘ በኋላ፣ የኢትዮጵያን እየተለወጠ የመጣውን የባህር ላይ እና የጂኦ-ፖለቲካ ስትራቴጂ እንመረምራለን። ለዚህም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር ከሆኑት ከአቶ በላይ በየነ ጋር በዝርዝር እንቃኛለን።
በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ በደቡባዊው ዓለም ወስጥ በመካሄድ ላይ ስላለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢ- ሞቢሊቲ) አብዮት እንዳስሳለን። ለዚህም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመካኒካል፣ ኬሚካል እና ማቴሪያል ሳይንስ ምህንድስና ኮሌጅ ዲን ከሆኑት ከዶ/ር ሽመልስ ለማ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
