Episode Description
“የወደብ አጠቃቀም ሶስት አይነት ናቸው፡፡ አንደኛ አብሮ በማልማት፣ ሁለተኛ በሊዝ ኪራይ፣ ሶስተኛ ደግሞ ይዞታ በመለዋወጥ ነው፡፡ እና ይሄንን ማድረግ የምንችልበት መደራደር፣ መነጋገር፣ መወያየት እና መቀራረብ ነው፡፡ ስለዚህ ያነሳነው ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እኛ ብቻ እንጠቀም አላልንም፡፡ እነሱም ይጠቀሙ ነው፡፡” ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰላምና የዉጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር መውጫ ለማግኘት ያቀረበቸውን ጥያቄ እና የምታደርገውን ጥረት በጥልቀት እንመረምራለን። በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰላምና የዉጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ቶፊቅ አብዱላሂ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ይህን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፣ ደኅንነትና የክልላዊ ሁኔታ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ የሚያሳድረውን ጉዳይ እንዲሁም በዓለም አቶሚክ ሳምንት ስብሰባ የኢትዮጵያ ተሳትፎን ማዕከል አድርገን የዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች አንቂ እና በአለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያ ተወካይ ከሆነው ከወጣት ኑርሁሴን አሊ ጋርም ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
