የአፍሪካን የእንስሳት ሀብት ማዘመን፡- ከምርታማነት እስከ አህጉራዊ እሴት ሰንሰለት

July 21
1 hr

Episode Description

"እኛ የምንፈልገው የተቀናጀ አህጉራዊ የእንስሳት ሀብት እሴት ሰንሰለትን መፍጠር ነው። ከአምራቹ ጀምሮ እስከ እሴት መጨመር እና ማቀነባበር ድረስ ያሉትን ሂደቶች በሙሉ በመደገፍ፤ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የስጋ እና የወተት ምርቶችን በራሳችን አህጉር ለማምረት የግል ባለሀብቱን ማሳተፍ ይኖርብናል።" ሲሉ በአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ እንስሳት ሀብት ቢሮ (AU-IBAR) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሁያም ሳሊህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ በቀዳሚነት ከአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ እንስሳት ሀብት ቢሮ (AU-IBAR) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሁያም ሳሊህ ጋር የአፍሪካን የአርብቶ-አደር ማህበረሰብ ኢኮኖሚ ከዕለት-ጉርስ ኑሮ ወደ አህጉራዊ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ሞተርነት ስለማሸጋገር ያደረገነውን ውይይት እናቀርባለን።

በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በሐምሌ ወር 2026 እ.ኤ.አ የተካሄደው 23ኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር አመታዊ ጉባኤ መነሻ አድርገን ከማህበሩ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና፣ ከከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎቹ አሰፋ አድማሴ (ዶ/ር) እና አቡሌ መሀሪ (ዶ/ር) ጋር፤ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዎችን የመቋቋም አቅም፣ የብሪክስ (BRICS) እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ዕድሎች በጥልቀት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ 

See all episodes