የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት፦ ከጥሬ ዕቃ ወደ ማኑፋክቸሪንግ እና የሴንትፒተርስበርግ ጉባዔ ሚና

June 4
1 hr

Episode Description

“ለአፍሪካውያን የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባር የገዛ ቤታችንን ማስተካከል ነው። ወደ እነዚህ ዓለም አቀፍ መድረኮች የምንሄደው የምንሸጠውን ነገር ሳንለይና ሳናደራጅ መሆን የለበትም፤ የሌለንን ነገር ለመሸጥ መሞከር ዘበት ነው። በመጀመሪያ የተፈጥሮ ሀብታችንን እና የፋይናንስ መዋቅራችንን በራሳችን ማደራጀት አለብን። ይህንን ካደረግን ወደ መድረኩ የምንመጣው በበላይነት እና በጥንካሬ ነው፤ ያለበለዚያ ግን፣ ውይይቶቹን ስንከታተል እንደምናየው፣ የምንሄደው ሁልጊዜ የእርዳታ እና የችሮታ ልመና ሰነድ ይዘን ብቻ ይሆናል።” ሲሉ በማላዊ ብሔራዊ የፕላኒንግ ኮሚሽን የልማት ኢኮኖሚስት የሆኑት ኦስቲን ቺንግዌንግዌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት መጀመሪያ ክፍል ከሰኔ 03 እስከ ሰኔ 06፣ 2026 እ.ኤ.አ. የሚካሄደውን የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረምን (SPIEF 2026) እንቃኛለን። የአፍሪካን አንድ ወጥ አህጉራዊ ድምፅ፣ አማራጭ ክፍያዎችንና ማዕቀብን የመቋቋም ዕድሎችን በማላዊ ብሔራዊ የፕላኒንግ ኮሚሽን የልማት ኢኮኖሚስት የሆኑት ኦስቲን ቺንግዌንግዌ ያብራራሉ።

በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር አህጉሪቱን ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ማኑፋክቸሪንግና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስለማሻገሩ እንዲሁም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ስለማስከበሩ እና የሴንት ፒተርስበርግዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ሚናን እንቃኛለን ለዚህም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና መምህር ከሆኑት ከ መሐመድ ሙሳን (ዶ/ር) ጋብዘናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:


See all episodes