የአፍሪካ ሉዓላዊነት በፖሊሲ ነጻነት እና በጤናው ዘርፍ

July 21
1 hr

Episode Description

"አፍሪካውያን መሪዎች በመጨረሻ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ለማን ነው? ለገዛ ዜጎቻቸው ወይስ ለውጭ አጋሮቻቸው? መንግሥታት ለውጭ የፖሊሲ መመሪያዎች፣ ለገንዘብ ድጋፎች ወይም ለአለም አቀፍ ተቀባይነት ቅድሚያ ሲሰጡ፤ የገዛ ዜጎቻቸውን የዕለት ተዕለት ችግሮች የመፍታት ኃላፊነታቸውን የማዳከም አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ።" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የለሴጎ ፋውንዴሽን (Lesego Foundation) መሥራች የሆኑት ሱቡሲሶ ማሻባኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ፦ በውጭ ዕርዳታና ድጋፍ ላይ ጥገኛ መሆን በአገር በቀል ተጠያቂነት ላይ የሚያስከትለው ዋጋ ምንድን ነው? የውጭ ጥገኝነት በአስተዳደር፣ በኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በኢንዱስትሪ ልማት እና በሥራ አጥነት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ከሱቡሲሶ ማሻባኔ ጋር በሰፊው እንወያያለን።

በክፍል ሁለት፦ የአፍሪካን የሕክምና ትምህርት እና የጤና ሥርዓትን ከአህጉሪቱ ነባራዊ እውነታዎች ጋር እንዴት ማጣጣም ይቻላል? ስንል በዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ቢሮ የጤና ሥርዓት እና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር አደልሄድ ኦንያንጎ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

See all episodes