የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ዋስትና በኢትዮጵያ፦ ከፖሊሲ ወደ ተግባር

May 28
1 hr

Episode Description

"የምግብ ስርዓት የምንለው ከምርት ጀምሮ እያንዳንዱ ሂደት አልፎ ምግብ የሸማቹ አፍ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሰንሰለት ነው።... የአየር ንብረት ለውጥ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ የዕሴት ሰንሰለቱ ላይ ምርታማነትንና ፍጆታን አደጋ ላይ የሚጥሉ መዛባቶችን እየፈጠረ ነው። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ሥርዓት መገንባት ማለት ሥርዓቱ እነዚህን አስደንጋጭ ክስተቶች መቋቋም እንዲችል ማድረግ ነው፤ በዚህም የቤተሰብን ኑሮ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በዘላቂነት ማስቀጠል ይቻላል።" ሲሉ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር (ዶ/ር ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

የአየር ንብረት መዛባት እና የአፈር መጎሳቆል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አነስተኛ አራሾችን ህልውና እየፈተኑ ይገኛሉ። ታዲያ ግብርናን ከምርት መጨመር ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም፣ ዘላቂነት እና ሉአላዊነትን ባገናዘበ መልኩ እንዴት መቅረፅ እንችላለን? የፖሊሲ ማዕቀፎችስ በምድር ላይ ያለውን እውነታ በትክክል እያስተናገዱ ነው?

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ቆይታ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጃ ያድምጡ ፡  


See all episodes