Episode Description
“ገንዘቡ እንደ አስፈላጊነቱ ከተለቀቀ ችግሩ የዋጋ ንረትን ያባብሳል። ህዝቡ የዋጋ ንረት መሸከም አይችልም። በተለይ ቋሚ ገቢ ያላቸው።” ሲሉ የዘመን ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር አቶ መሰረት ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የዘመን ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር ከሆኑት ከአቶ መሰረት ወንድም ጋር በመሆን የ[ኢትዮጵያ]ብር ምንዛሬ ለውጥ፣ ለገንዘብ ፍሰት፣ ለብድር እና ህዝቡ በፋይናንስ ሴክተሩ ስርዓቱ ላይ ያለው እምነት ላይ ምን ሊፈጥር እንደሚችል የዳሰስን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ የዲጂታል አስተዳደር እና ትራንስፎርሜሽን አማካሪ ከሆኑት ከአቶ እስክንድር ቸርነት ጋር፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስርዓቶች በስተጀርባ ያሉትን እና ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጣቸውን መዋቅሮች እንቃኛለን፡፡