Navigated to የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር፣ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ያገኙት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች

የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር፣ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ያገኙት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች

September 22
58 mins

Episode Description

“ይሄ ምርት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እና በአፋር ክልል ተሸጦ በቆላና መስኖ አካባቢ ሚኒስቴር ገዢነት ወደ ሁለቱ ክልል ቴክኖሎጂው እንዲተገበር ተደርጎ ሁለቱም ክልል ላይ ቴክኖሎጂውን ሰርተን አምርተን ገጥመንላቸው እየተጠቀሙ ነው።” በግብርና ዘርፍ በሰራው ስራ የወርቅ ተሸላሚው ዘላለም እንዳለው

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቅርቡ ከብሪክስ አባል ሀገራት በተውጣጡ 300 ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች መካከል በቻይና በተካሄደው የብሪክስ የ2025 የክህሎት ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ዘርፎች በመሳተፍ የወርቅ፣ የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ ከተሸለሙት ሶስት ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያ ወጣቶች ከዘላለም እንዳለው፣ አቤኔዘር ተከስተ የብር ተሸላሚ እና ነቢሀ ንስሩ የነሃስ ተሸላሚ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ወጣቶቹ በውድድሩ ላይ ይዘው ስለቀረቧቸው የፈጠራ ስራዎች፣ በውድድሩ ላይ ስለገጠሟቸው ነገሮች እንዲሁም ወደፊት ስላሏቸው ራዕዮች በሰፊው ተወያይተናል፡፡

ሙሉውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.