የቤተሰብ ዕቅድ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ከእርዳታ ጥገኝነት ነጻ የማድረግ ጅምር በኢትዮጵያ

February 20
1 hr

Episode Description

“የጤናውን ሴክተር ስንመለከት ጤና ብቻውን በአንድ የሚቆም።[…] የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ 'Health in All Policies' ነው የሚለው። የጤና ፖሊሲዎች በሁሉም ፖሊሲዎች ውስጥ መኖር አለባቸው። ምክንያቱም ግብርና ብንለው፣ ትምህርት ብንል፣ ሁሉም ብንላቸው የጤና ፖሊሲ ከሌላቸው ሙሉ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ዋናው ጤና ስለሆነ ማለት ነው።” ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በመጀመሪያው ክፍል በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ከሆኑት ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ጋር በመሆን መንግስት ከመደበኛ ብሄራዊ በጀቱ ወደ 14 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለፕሮግራሙ በመመደብ ከእርዳታ ጥገኝነት ነጻ የሆነ የጤና ስርዓትን እውን የማድረግ ሂደት እንመለከታለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች እድገት እና እየጨመረ ስለመጣው የቤት ፍላጎት ጉዳይ በሪል ሰቴት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ የማርኬቲንግ ባለሙያ እና አማካሪ ከሆኑት ኢንጂነር ቸርነት መንግስቴ ጋር ያደረግነውን ውይይት አካትተናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.