የስፔስ ቴክኖሎጂ፡ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊና መጻኢ እድል

August 21
1 hr

Episode Description

"የስፔስ ቴክኖሎጂ እዚሁ ቤታችን ነው፣ አጠገባችን ነው ያለው። ግብርናችን ጋር አለ። የምንሳፈርበት ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ አለ። የስፔስ ቴክኖሎጂ ያልገባበት ቦታ የለም።... ያለ ስፔስ ቴክኖሎጂ ወደፊት መሄድ አንችልም ማለት ነው።... ስለዚህ የስፔስ ቴክኖሎጂ ሁሉ ነገራችን እየሆነ መጥቷል።" ሲሉ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂዮስፓሺያል ኢንስቲቱት ም/ል ዋና ዳይሬክተር ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር)  ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታቸን አፍሪካ በህዋ ሳይንስ ያላትን አዲስ ምዕራፍ እና በምስራቅ አፍሪካ እየተገነቡ ያሉ ወታደራዊ ትብብሮችን በጥልቀት እንመረምራለን።  ክፍል አንድ፦ ዩሪ ጋጋሪን ወደ ህዋ ከመጠቀ ከ65 ዓመታት በኋላ፣ አፍሪካ በሳተላይት ቴክኖሎጂ ያላት ተሳትፎ የት ደረሰ? የኢትዮጵያ ETRSS 2 ሳተላይት ምጥቀትስ ለአህጉራዊ አጋርነት ምን ትርጉም አለው? በጉዳዩ ላይ ይሽሩን አለማየሁ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂዮስፓሺያል ኢንስቲቱት ም/ል ዋና ዳይሬክተር ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል። በክፍል ሁለት፦ የታሪክ ድርና ማግ! ኢትዮጵያና ታንዛኒያ ከ1950ዎቹ የጀመረውን ወታደራዊ ትስስር ዛሬ ላይ እንዴት እያደሱት ነው? የኢትዮጵያ አየር ኃይል የበላይነት ለቀጠናው ደህንነትና ለጸረ-ሽብር ትግሉ ያለው ፋይዳ ምንድን ነው? የሰላምና ጸጥታ እና የአካባቢ ጉዳዮች ተንታኙ አቶ ዮሴፍ ወልደኪዳን ማብራሪያ ይዘው ቀርበዋል። 


See all episodes