የስነ-ጽሁፍ ሚና በማንነት እና በታሪክ ንቃተ-ህሊና ግንባታ

August 21
1 hr

Episode Description

"ወደ ዘመናዊ ስነጽሁፍ ስንመጣ ዘመናዊ ስነጽሁፍ በአብዛኛው በቴክኒኩ የውጪውን ፈለግ የተከተለ ስለሆነ ኢትዮጵያዊነት አሻራን በቴክኒኩ ላይ ማግኘት ያስቸግራል፤ ያው በጭብጡ ወጣም ወረደ ኢትዮጵያዊ ባህል ነው፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው። ... በዚህ ረገድ ቃላዊ ግጥሙ፣ ቃላዊ ትረካው በተሻለ ደረጃ ማንነታችንን በማሳየት የጎላ ባህሪ አለው።" ሲሉ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ጽሁፍ መምህር የሻው ተሰማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በተጨማሪም "... ፖለቲካው ላይ ያለውን ትተነው፣ መሬት ላይ ያለው ማህበረሰብ ፍቅር አለው፣ መከባበር አለው፣ መተሳሰብ አለው፤ መረዳዳት አለው፤ መደጋገፍ አለው። የሰነ-ጽሁፍ ሥራዎቻችንም ይህን አጉልተው ማሳየት አለባቸው።" ሲሉ አክለዋል።

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዷችን በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጽሁፍ መምህር ከሆኑት የሻው ተሰማ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ የሀገርን ዳርቻ ከመጠበቅ ባለፈ የኢትዮጵያዊነትን እና የአፍሪካዊነትን መልክ በመቅረጽ ረገድ የነበረውን ሚና፣ እንዲሁም የሀገር በቀል ቋንቋዎችን ለስነ-ጽሁፍ ስራዎች መጠቀም የአስተሳሰብ ነፃነትን ለማረጋገጥ ያለውን ድርሻ እንቃኛለን። በተጨማሪም በቴክኖሎጂ መስፋፋት ምክንያት የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ የወደፊት እጣ ፈንታ እና ወደፊት የአፍሪካን አዲስ ትርክት በመገንባት ረገድ ሊኖረው የሚችለውን ሚና በዝርዝር እናቀርባለን።


See all episodes