የሰብአዊ እርዳታ ሉዓላዊነት፡- የሀገርን ነፃነትና ክብር የማስጠበቅ ተግባር

June 23
1 hr

Episode Description

"የሰብአዊ እርዳታ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አሁን ላይ ለማንኛውም ሀገር ምርጫ አይደለም፤ በተለይም ስለ ሀገር ክብር፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለሚያስብ ሀገር ይህ ጉዳይ የግድ የሚል ተግባር ነው።" ሲሉ የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 

በዚህኛው ባለ ሶስት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በመጀመሪያው ክፍል በአርኪኦሎጂ እና በሰው ልጅ አመጣጥ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የፓሊዮአንትሮፖሎጂ ተመራማሪዎች ከሆኑት ከዶ/ር በርሄ አስፋው እና ከዶ/ር ዮናስ በቀለ ጋር በመካከለኛው አዋሽ ስለተገኙ አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶች እንወያያለን።

በሁለተኛው ክፍል፤ የአፍሪካን የሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የመከላከል አቅም እንዲሁም ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት የመውጣት አስፈላጊነትን በተመለከተ ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ጋር የነበረንን ቆይታ እናቀርባለን።

በመጨረሻም አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ የምግብ ዋስትናዋን እንዴት ማረጋገጥ ትችላለች? በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ ከአፍሪካ ህብረት የግብርና እና ምግብ ዋስትና ክፍል ተጠባባቂ ሃላፊ ዶ/ር ጃኔት ኤደሜ እና ከAGRA የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር ይሄነው ዘውዴ ጋር ያደረግነውን ውይይት አካትተናል።


See all episodes