የሥነ-ምግባር ሉዓላዊነት፦ አፍሪካ የሞራል መሠረቷን ከምዕራባውያን ተፅዕኖ እንዴት ትጠብቅ?

May 7
1 hr

Episode Description

"ሥነ-ምግባር ለአንድ ማህበረሰብ ህልውናው ነው። አፍሪካ የራሷን የሞራል መሠረትና እሴቶች መጠበቅ ካልቻለች፣ በግሎባላይዜሽን ማዕበል ውስጥ ማንነቷን አጥታ የሌሎች እሴቶች ተገዢ ትሆናለች።"ሲሉ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት  ዶ/ር አባ መዝገቡ ካሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

የዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ሥነ-ምግባር ዓለም አቀፋዊ ነው ወይስ በባህልና በስልጣን የሚወሰን? የአፍሪካ ማህበረሰቦች የውጭ 'እሴቶችን' እየተቀበሉ ነው ወይስ ያለ ምርጫ እየተጫኑባቸው ነው ? ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤቶች እና የሃይማኖት ተቋማት የሞራል መሸርሸርን ለመከላከል ምን እያደረጉ ነው? ሲል ይጠይቃል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን ዶ/ር አባ መዝገቡ ካሳን ጋብዘናቸዋል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

See all episodes