Episode Description
“እነዚህ ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የምንላቸው ዋነኛ ቀጣሪ ሴክተር ናቸው፤ መተዳደሪያም ነው፤ ኢኮኖሚው የተረጋጋ እነዲሆን ያደርጋል፡፡ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ደረጃ የተለያዩ ነገሮች ለዝቅተኛ ማህበረሰብ በማቅረብ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው፡፡“ ሲሉ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር ውስጥ ተመራማሪ ዘነበች አድማሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚው ያለውን አስተዋጽዎ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር ውስጥ ተመራማሪ ዘነበች አድማሱ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ በተጭማሪም ስለ ኢትዮጵያ የማሪታይም ትምህርት በኢትዮጵያ ባህር ትራስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን የባቦጋያ ማሪታይም እና ሎጅስቲክስ አካዳሚ ዲን ከአቶ ሲራጅ አብዱላሂ ጋር ያደረግነው ውይይት በዚህ ዝግጅት ውስጥ ተካቷል፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፐሮግራሙን ያዳምጡ ፡