የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ስጋት

August 8
1 hr

Episode Description

"አሁን በዋነኝነት የጨመረው ነገር የኢንሹራንስ አረቦን ፣ የሴኩዩሪቲ ክፍያ እና የመሳሰሉት ናቸው... ከዚህ በፊት ሲከፈል የነበረውን ያህል ዋጋ መቶ ፐርሰንት በሚባል ደረጃ እጥፍ ሆኗል። ያ ደግሞ በተዘዋዋሪ የመጨረሻ ያለቀው መድሃኒት ላይ ዋጋ እንዲጨምር ያደርገዋል።" ሲል የፋርማሲ ባለሙያው አቶ በረከት ጌታሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ 

ከድንበራችን ባሻገር ያለው ጦርነት እቤትዎ ድረስ የሚደርስ የጤና ስጋት እየሆነ ነው?

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው አለመረጋጋት እና የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት እና ገበያ ላይ ምን እያደረሱ ነው? አቅርቦቶች ሲዘገዩ እና ዋጋ ሲጨምር የዜጎች ህይወት ምን ይሆናል?

በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ የፋርማሲ ባልሙያ ከሆነው ከአቶ በረከት ጌታሁን ጋር የዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት መቆራረጥ በብሔራዊ የጤና ደህንነታችን ላይ የደቀነውን አደጋ በጥልቀት እንመረምራለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ፡


See all episodes