Episode Description
“ከውጭ ነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት የተቀናጀ ስትራቴጂ ያስፈልጋል። ትኩረታችንን የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማትን በማዘመን፣ በፀሐይ ኃይል እና በአገር ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት ላይ በማድረግ የኢነርጂ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል።” ሲሉ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ወስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ጀማል መሀመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ከነዳጅ ፖለቲካ እስከ ቀጠናዊ ደህንነት፦ ኢትዮጵያ በአዲሱ የዓለም የኃይል አሰላለፍ ውስጥ!
በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን ሁለት አንገብጋቢ ጉዳዮችን ከባለሙያዎች ጋር በጥልቀት እንመረምራለን፦
የነዳጅ ጂኦ-ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ፈተና፦ የዓለም የነዳጅ ገበያ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጥረውን ጫና እና ሀገሪቱ የጀመረችው የጋዝ ተሽከርካሪዎች (Natural Gas Conversion) ሽግግር እንደ መፍትሄ ሊታይ ይችላል? የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ጀማል መሀመድ ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል።
የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ወታደራዊ ትብብር፦ ሽብርተኝነትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል በኢትዮጵያ እና በታንዛኒያ መካከል እየተገነባ ያለው ወታደራዊ ግንኙነት በቀጠናው የኃይል ሚዛን ላይ ምን ለውጥ ያመጣል? የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልናስር ምዊታ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን እይታ ያካፍሉናል።