Navigated to ካሪኮም (CARICOM)፣ ብሪክስ (BRICS)፣ እና ለፍትሐዊ ዓለምአቀፍ ሥርዓት የሚደረግ ጥረት

ካሪኮም (CARICOM)፣ ብሪክስ (BRICS)፣ እና ለፍትሐዊ ዓለምአቀፍ ሥርዓት የሚደረግ ጥረት

September 30
1 hr

Episode Description

“የምንጠይቀው ገንዘብ እንዲሰጠን ብቻ አይደለም። ከፍተኛ የሆነ የዕዳ ሸክም የመጣው ከረጅም ጊዜ የባርነት ታሪክ ጋር በተያያዘ መሆኑን እውቅና እንዲሰጥ እንጠይቃለን። ስለዚህ፣ ዛሬ ያለውን ሁኔታ የካሳ ፍትሕ ለማምጣት ሲባል ዕዳው የሚተውበት ጊዜ ደርሶ ሊሆን ይችላል። የምንጠይቀው ይህን ነው።” ዶ/ር ዴንዚል ዳግላስ የሴንት ኪትስ እና ኔቪስ የውጭ ጉዳይ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በአፍሪካ እና በካሪቢያን መካከል ለፍትህ የሚደረገው ትግል ምን ያገናኛቸዋል? የሚለውን ለመዳሰስ ከሴንት ኪትስ እና ���ቪስ የውጭ ጉዳይ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ዴንዚል ዳግላስ ጋር ተወያይተናል። እንዲሁም የካሳ ጥያቄዎች፣ የቅኝ ግዛት ውርስ እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር መነሳት በሰፊው ይዳሰሳሉ።          ከፓን-አፍሪካኒዝም አንስቶ እስከ ብሪክስ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሻሻያ ድረስ፣ የደቡባዊው ዓለም የወደፊት ዕጣ ፈንታ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዴት መቀረጽ ይገባዋል የሚሉ ጉዳዮችም አንስተናል። በዚሁ መሰናዶ ዓለማአቀፉን የትርጉም ቀን መነሻ አድርገን ኢትዮጵያዊውን እዉቅ ተርጓሚ ጋሽ ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም  እና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የትርጉም ባልሙያ የሆነችውን ሳኖማ ኬሎግን ከትርጉም ስራዎች ጀርባ ስላሉ የባህል ውርርሶችና ልዩ መልኮቹም አነጋግረናቸዋል፡፡ 

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡


See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.