ከጂኦፖለቲካ እስከ ጤና ስርዓት፤ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጉዞ

July 11
1 hr

Episode Description

"ቻይናውያን በታሪካቸው... መሬት ለመቀማት ወታደራዊ ካምፖችን ወይም ሰፈሮችን ለመመስረት አልመጡም። ይህንን ያደረገው አንድ የወራሪዎች ቡድን ብቻ ነው—በተለይም እንግሊዞች፤ አሁን ደግሞ አሜሪካውያን ይህንን የብሪታንያን ባህሪ ወርሰውታል።" ሲሉ ኬንያዊው የህግ ባለሙያውና የ2023 ሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ተወካይ አህመድ አብዱልአዚዝ ካዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ በመጀመሪያው ክፍል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ ቢኖርም እንግሊዝ የቻጎስ ደሴቶችን ለሞሪሸስ አለማስረከቧ በአለም አቀፍ ህግና ሉዓላዊነት ላይ ስለደቀነው ስጋት፤ ከህግ ባለሙያውና ከሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ተወካይ አቶ አህመድ አብዱልአዚዝ ካዲ ጋር ሰፊ ቆይታ አድርገናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ የሚያዝያ 28 ቀን 2026 እ.ኤ.አ የተካሄደውን አምስተኛው ዓለም አቀፍ የመድሐኒት አቅራቢዎች ጉባዔን መነሻ አድርገን ኢትዮጵያ በመድኃኒት አቅርቦት ራሷን ለመቻልና ቀጣናዊ ማዕከል ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ በተመለከተ፤ ከኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እና ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ተፈሪ ጋር ያደረግነውን ውይይት እናቀርባለን። 

በመጨረሻም በአፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም እና የፋይናንስ ክፍተቶች ዙሪያ፤ ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የመሰረተ ልማትና አጋርነት ምክትል ፕሬዝዳንት ፌሊክስ አሮሜ እና ከሞሪሸስ የግብርናና ምግብ ዋስትና ሚኒስትር ዴኤታ ጊልስ ፋብሪስ ዴቪድ ጋር የነበረንን ቆይታ አካትተናል። 

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ: 

See all episodes