ከዲጂታል ጥገኝነት ወደ ዲጂታል ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ፈተና

June 29
1 hr

Episode Description

"ለእኔ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማለት ቴክኖሎጂን መግዛት ብቻ አይደለም፤ ቴክኖሎጂውን እንዴት እንደምንጠቀምበት፣ የዜጎችን ዲጂታል ሀብት እንዴት እንደምንጠብቅበት እና ማኅበረሰቡን እንዴት እንደሚያገለግል መቅረጽም ነው። […] አፍሪካ የራሷን የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፍ ካልገነባች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የቅኝ ግዛት ሰለባ የመሆን አደጋ አለ።" ሲሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በተጨማሪም "ገንዘብ ካለህ ቴክኖሎጂን በአንድ ሌሊት መግዛት ትችላለህ፤ ነገር ግን ዲጂታል ብቃት፣ የሰው ኃይል አቅምና ተገቢ የአስተዳደር ሥርዓት ያለ ቴክኖሎጂ በማይበቅል መሬት ላይ ዘር እንደመበተን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ከቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እንዲሁም የCloud Security Alliance Ethiopia Chapter የቦርድ አባል ከሆኑት ከአቶ እስክንድር መስፍን ጋር፣ አፍሪካ ከዲጂታል ጥገኝነት ወጥታ እውነተኛ ዲጂታል ሉዓላዊነትን እንዴት ልትገነባ እንደምትችል በስፋት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦



See all episodes