Episode Description
“ችግሩ የአፍሪካውያን የአእምሮ ወይም የፈጠራ አቅም ማነስ አይደለም፤ በፈጠራችን የበለፀግን ነን። ዋናው ተደቅኖብን ያለው ፈተና የትምህርትና የምርምር ሥርዓታችን ታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ለአዲስ ፈጠራ ይልቅ ለእውቀት ማስተላለፍ ብቻ ተቀርጾ መቆየቱ ነው።” ሲሉ በርቀት ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አደራጀው ምህረት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በተጨማሪም “የአፍሪካ የወደፊት ተወዳዳሪነት የሚወሰነው ምን ያህል እውቀት እንመገባለን (ንባብና ትምህርት ላይ ብቻ እንደርሳለን) በሚለው ሳይሆን፤ ምን ያህል እውቀትን ውጤታማ በሆነ መንገድ እናመርታለን፣ እንተግብራለን፣ እንዲሁም ለዓለም እናካፍላለን በሚለው ላይ ነው።”ሲሉ አክለው አብራርተዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከአደራጀው ምህረት (ዶ/ር) ጋር በመሆን አፍሪካ ለወደፊቱ ትውልድ የሚያስፈልጋትን መፍትሔ አውጪ እና ፈጠራ ታከለበት የትምህርት ፍልስፍና እንዴት መገንባት እንዳለባት በጥልቀት እንወያያለን።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡