ከአፍሪካ ሉዓላዊነት እስከ ባለብዙ-ዋልታ ዓለም

July 11
1 hr

Episode Description

"ይህ (በሀገር ውስጥ ምንዛሬ የመገበያየት ሞዴል) አገሮችን በፋይናንስ ማዕቀብ ከሚያስረው ስዊፍት [Swift] የክፍያ ስርዓት ለመውጣት ጥሩና ውጤታማ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ሞዴል የደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ሀብት በምዕራባውያን ኃይሎች እጅ እንዲያዝ እና እንዲወረስ ተጋላጭ ከማድረግ ይልቅ፣ እዚሁ በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ውስጥ ተከማችቶ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል መንገድ ይከፍታል።" ሲሉ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እ.ኤ.አ በግንቦት 19 እና 20 ፣ 2026 ወር አጋማሽ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት ተከትሎ ሞስኮ እና ቤጂንግ የፈረሙት ታሪካዊው የጋራ መግለጫ ለአዲሱ የዓለም የኃይል ሚዛን ምን ትርጉም አለው? የሚለውን የምንቃኝ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ በየዓመቱ ግንቦት 17 የሚከበረውን የአፍሪካ ቀን ለአህጉሪቱ እውነተኛ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ምን አዲስ ጥያቄዎችን እና የቤት ስራዎችን ይዞልን መጥቷል? የሚለውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናት ማዕከል መምህር ጌታቸው ካሳ(ዶ/ር) እና የታሪክ እና ቅርስ ጥበቃ ስርአተ-ትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ ተረፈ ወርቁ ጋር ተወያይተንበታል፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:  

See all episodes