Episode Description
"አፍሪካ የራሷን የአእምሮ ነጻነት ማረጋገጥ ካለባት፣ የትምህርት ሥርዓቱ በሌላ ሀገር በተቀረጸ የተውሶ መዋቅር ላይ ሳይሆን፣ በራሷ ነባራዊ እውነታዎችና ምኞቶች ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ማዕቀፍ ሆኖ እንደገና መነደፍ አለበት። የአፍሪካን አእምሮ ነጻ ማውጣት ማለት ፊታችንን ከዓለም ማዞር ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በዚያ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በገዛ የራሳችን ድምፅና ማንነት መቅረብ መቻል ማለት ነው::" ሲሉ የርቀት ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አደራጀው ምሕረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ ለዲጂታሉ ዘመን የሚመጥን እና ከአውሮፓውያን የተውሶ አስተሳሰብ የወጣ የአገር በቀል ትምህርት ፍልስፍናን በአፍሪካ እንዴት መቅረጽ ይቻላል? የርቀት ትምህርት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአህጉራዊ የዕውቀት ሉዓላዊነት እንዴት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው? በጉዳዩ ላይ ረዳት ፕሮፌሰር አደራጀው ምሕረት ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል። በክፍል ሁለት የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ለአፍሪካ እና እስያ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎችና ምሁራን የሚጥሉት የቪዛ እገዳ በዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪነት መድረኮች ላይ እኩል ውክልና እንዳይኖር እያደረገ ያለው እንዴት ነው? ይህስ የአፍሪካን ዕውቀትና አቅም ካለማክበር ጋር ምን ትስስር አለው? ናይጄሪያዊው የማኔጅመንት ባለሙያ አደፖጁ ፎዎካን ጋር ያደረግነውን ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ: