ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሀብት ፈጣሪነት፦ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓትና የዕውቀት ነጻነት

July 11
1 hr

Episode Description

"የትምህርት ሥርዓታችን አሁንም ድረስ የራሳቸውን ሀብት የሚፈጥሩ ሉዓላዊ ዜጎችን ከመቅረጽ ይልቅ በሌሎች ላይ ጥገኞች የሆኑ የሥራ ፈላጊዎችን ስብስብ እያመረተ ይገኛል።... እውነተኛ ነጻነት የሚጀምረው የአፍሪካን የአገሬው ተወላጅ ዕውቀቶች እና ቋንቋዎች ለኢኮኖሚና ለዕውቀት ነጻነት ማዋል ስንችል ነው፡፡" ሲሉ የሌሴጎ ፋውንዴሽን መሥራች ሲቡሲሶ ማሻባኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። 

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ተላቆ አዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎችን ለማፍራት መከተል ስላለበት የዕውቀት ምንጭ ከደቡብ አፍሪካው የለሴጎ ፋውንዴሽን መሥራች ከሲቡሲሶ ማሻባኔ ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ውይይት ይዘን ቀርበናል። ክፍል ሁለት ደሞ አዲሱ ብሔራዊ የቱሪዝም ፖሊሲና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ለመሳብ ስላለው ዕቅድ፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ ከሰኔ 20 እስከ ሰኔ 24 ፣ 2026  በኢትዮጵያ የቱሪስት አስጎብኝዎች “ኢትዮጵያ በቱሪስት አስጎብኝዎች ዓይን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሙዚየም ለዕይታ የቀረበውን 4ኛው የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይን እንዳስሳለን። ዐዉደ ርዕዩ ቱሪዝምን ለማነቃቃት ስላለው ሚና የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ እና የኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ጸጋዬ ማብራሪያ ይሰጡናል።

See all episodes