ከመገኛነት ወደ ጠንካራ የምርት መለያነት፦ የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና በአለም አቀፍ መድረክ

June 3
1 hr

Episode Description

"የኢትዮጵያ ቡና ከሰራነው በላይ ፈጣሪ የሰጠን ትልቅ ሀብት ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ቡና ከአለም ቢጠፋ፣ ቡና ከአለም ላይ እንደሚጠፋ ያውቃሉ? ምክንያቱም የቡና ዝርያ ክምችቱና (Genetic Reserve) መሰረቱ ያለው እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግዛት ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የዋጋ አለመረጋጋት እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የኢትዮጵያን የቡና ኤክስፖርት እንዴት እያስተጓጎለ ይገኛል? ይህስ ለውጭ ምንዛሬ፣ ለኑሮ ሁኔታ እና ለገበያ መረጋጋት ምን ትርጉም አለው? በሚሉ ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ግዛት ወርቁ ጋር የተወያየን ሲሆን፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት (UNHRC) በሩሲያ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ መሰረት አድርገን ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ከሆኑት ከአቶ አንዱዓለም በውቀቱ ጋር የሰብአዊ መብቶች ስርዓት ስለተደቀነብት ፈተና ያደረግነውን ውይይት በሁለተኛው የመሰናዶአችን ክፍል አካትተነዋል፡፡


See all episodes