ከመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እስከ አህጉራዊ ደህንነት፦ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዴት ለአፍሪካ መከታ ሆነ?

August 26
1 hr

Episode Description

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት፣በቀይ ባህር አቅራቢያ የሚታየው የውጭ ኃይሎች ወታደራዊ መገኘት እና የባህርላይ የንግድ መስመሮች መስተጓጎል በምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚና ደህንነት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድንነው? ስንል በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) አስተያየታቸውን አጋርተውናል።

ከታሪካዊው የአድዋ ድል እስከ ዘመናዊው የኒዮ-ኮሎኒያሊዝምተፅዕኖ እና የ '' ኖ ሞር እንቅስቃሴ'' የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስከበር የመላው አፍሪካን ነፃነት እና ክብር የማስጠበቅ ያህል የሚቆጠረው ለምንድንነው? ስንል ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ አህመድ ዘካሪያን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ እና ታሪካዊ ትንተና ይሰጡናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:


See all episodes