ኢነርጂ፣ ኢንቨስትመንትና የሩሲያ ቴክኖሎጂ፦ የኢትዮጵያ የኑክሌር ጉዞ

June 23
1 hr

Episode Description

"የኑክሌር ኃይል ማመንጫ መገንባት ሀገሪቱ አስተማማኝ እና ቋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ እንድታገኝ ያስችላታል። […] ይህ አሠራር ደግሞ ድርጅቶችና ፋብሪካዎች ያለምንም መቆራረጥ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር በር ከፋች ነው። እንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶችን መተግበር በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ዋነኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል::" ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድ ተወካይ ያሮስላቭ ታራሲዩክ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። 

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከብሪክስ አባልነት በኋላ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያና የሩሲያ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ የንግድ ዕድሎችን እና አዳዲስ ሳይንሳዊ ትብብሮችን በጥልቀት እንመረምራለን። በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድ ተወካይ አቶ ያሮስላቭ ታራሲዩክ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡናል። በክፍል ሁለት ደግሞ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሕ/ተ/ም/ቤት ያጸደቀው የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ባዮሎጂካል ምርምር ማዕከል ስምምነት ለሀገሪቱ የብዝሃ-ሕይወት ጥናት፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለከፍተኛ ትምህርት ዕድገት ምን ፋይዳ አለው ስንል በም/ ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ መህዲ ማብራሪያ ጠይቀናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

See all episodes