Navigated to ኃይል ወይስ ሕግ፦ ተመድ አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነውን?

ኃይል ወይስ ሕግ፦ ተመድ አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነውን?

January 27
1 hr

Episode Description

“የቪቶ (ድምፅን በድምጽ የመሻር) ስልጣን ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፤ ተበድሏልም። በ2003 በኢራቅ ላይ በአሜሪካ ጥቃት ሲሰነዘር ሩሲያ ለዚያ ወረራ እና ወታደራዊ ጣልቃገብነት ድምፅ አልሰጠችም። […] አፍሪካ በ2026 ያላትን ቋሚ ያልሆኑ መቀመጫዎች ብንመለከት እንኳ፣ የቪቶ ስልጣን ባላቸው አምስቱ ቋሚ አባላት እና የቪቶ ስልጣን በሌላቸው ቋሚ ባልሆኑ አባላት መካከል ያለው ልዩነት ምንም አይነት ትርጉም አይሰጥም። ይህ ሁኔታ በእውነቱ ዓለም አቀፍ ህግን መሳቂያ ያደርገዋል።” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒሳ የታቦ ምቤኪ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሌጅ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ራስ አድቮኬት ሲፎ ማንቱላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የቬንዙዌላን ጉዳይ ማዕከል አድርገን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሁንም በሕግ የሚመራ ተቋም ነው—ወይስ ዓለም አቀፋዊ አስተዳደር የኃይል እና የመራጭነት (አድሏዊ) አፈጻጸም ጨዋታ ሆኗል? የሚለውን ጥያቄ በደቡብ አፍሪካዉ የታቦ ምቤኪ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሌጅ ውስጥ ተመራማሪ ከሆኑት ከራስ አድቮኬት ሲፎ ማንቱላ ጋር በሰፊው እንመረምራለን። በተጨማሪም አንዳንድ አገራት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ሕጋዊነታቸው እንዲታጣስ ሲደረግ፣ ሌሎች ደግሞ ጥበቃ የሚደረግላቸው ስለምንድን ነው? ይህስ በጂኦ-ፖለቲካዊ ሽኩቻ በተቀረጸው ዓለም ውስጥ ስለ ሉዓላዊነት ምን ይነግረናል? የሚሉትንም ጥያቄዎች እንዳስሳለን፡፡

እንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes

Never lose your place, on any device

Create a free account to sync, back up, and get personal recommendations.