Episode Description
"ውኃ ለአፍሪካ እና ለአፍሮ-ዲያስፖራው ከቀላል የተፈጥሮ ሃብትነት ባለፈ፣ አህጉራትንና ትውልዶችን የሚያገናኝ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ድልድይ ነው። ሳይንስን ከባህል፣ ቴክኖሎጂን ከአካባቢያዊ እውቀት ጋር በማጣመር የአየር ንብረት መረጃ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ እና በግሎባል ሳውዝ አገራት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር ይኖርብናል፡፡" ሲሉ የኢትዮጵያ ኦሽን ኢንስቲትዩት ተባባሪ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኪዳን ኒኪታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛውየራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ "የሰማያዊ ኢኮኖሚዎችን ማስተሳሰር፦ አፍሪካን እና አፍሮ-ዲያስፖራን በውኃ ማገናኘት" በሚል ዋና ርዕስ ዙሪያ የውቅያኖስ ሳይንቲስት እና የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ባዮሎጂስት ከሆኑት ከኪዳን ኒኪታ ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግን ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር እና ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በድጋሚ በባረቁበት በዚህ ወቅት፣ ያልተማከሉ የሳይንስ ግኝቶች፣ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች "Lab in a Bag" እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር ምን ያህል ለውጥ እያመጡ እንደሆነ እንቃኛለን። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የሰማያዊ ፣ የአረንጓዴ እና የፈጠራ/የካሮት ኢኮኖሚዎች ትስስር ለአፍሪካ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ እና ለአካባቢ መላመድ ያለውን ወሳኝ ሚና በዝርዝር ዳሰናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጃ ያድምጡ ፡