Episode Description
"ምርምርን በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ውስን ሀብት ባለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለልማት 'የአቅም ማባዣ' (force multiplier) አድርጌ እገልጸዋለሁ። ሀብት ውስን በሚሆንበት ጊዜ ዋናው ፈተና የሀብቱ እጥረት ሳይሆን ያንን ያለውን ሀብት ምን ያህል በብቃትና በአግባቡ እየተጠቀምንበት ነው የሚለው ነው። ምርምር እጅግ ወሳኝ የሚሆነውም እዚህ ቦታ ላይ ነው።" ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፋከልቲ ከፍተኛ የምርምር ባለሙያ ሰለሞን አስማረ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም "ዩኒቨርሲቲዎች የሚያሳትሟቸው የምርምር ውጤቶች ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡ ይህ መጣጣም ሲኖር የህብረተሰቡን ችግር በመቅረፍ ረገድ እንዲሁም ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ በሁለቱም በኩል መዋቅራዊ እና አሰራራዊ ለውጥ ያስፈልጋል።" ሲሉ አክለዋል፡፡
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን በከፍተኛ የምርምር ባለሙያው ሰለሞን አስማረ አማካኝነት ምርምር ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት ያለውን ፋይዳ፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር የሚቻልባቸውን መንገዶች፣ እንዲሁም የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሚና እንመለከታለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡