ሁለት የልማት ግንባሮች፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን መዋጋትና ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት

March 24
1 hr

Episode Description

"አብዛኞቹ ለቲቢ የምንጠቀማቸው መድኃኒቶች ከውጭ የሚገቡ ናቸው። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስወጣናል። ለውጭ ተፅዕኖ ተጋላጭ የሆንነውም ለዚህ ነው። ስለዚህ፣ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን የምናጎለብትበት ዕድል ካገኘን፣ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ የሚያስከትለውን ችግር መቋቋም እንችላለን። ለአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች የራሳቸውን የምርመራ መሣሪያዎችና መድኃኒቶች ማምረት እንዲችሉ አቅማቸውን ማጠናከር ይገባል።" ሲሉ የ 'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በቀዳሚነት መጋቢት 15 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሳንባ ነቀርሳ ቀንን በማሰብ በሩሲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሳንባ ነቀርሳ ዋና አማካሪ ስፔሻሊስት ከሆኑት ከኢሪና ቫሲሊየቫ እንዲሁም የቪ.ኤች.ኤስ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከአቶ እንደአልካቸው ፍቃዱ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የሳንባ ነቀርሳ ከድህነት፣ ከጤና ሥርዓት እና ከማኅበራዊ እውነታዎች ጋር እንዴት እንደሚገናኝ እንቃኛለን፤ በማስከተልም፣ በ10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲ ፍሎራ ኤክስፖ ላይ ተገኝተን ከኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ እና ከአቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ የኢትዮጵያ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ለኢኮኖሚው ያለውን ሚና እንዳስሳለን፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

See all episodes