የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ነው ?

May 28
1 hr

Episode Description

''ዋሽንግተን መሪዎችን በመግደል እና ኃይሏን በመጠቀም ኢራንን በአጭር ግዜ ውስጥ አንበረክካለሁ ብላ አስባ ነበር። በተቃራኒው ኢራን ድብደባዎቹን ተቋቁማ፤ መከላከሏን ቀጠለች እንዲሁም የጦር ሜዳውን ወደ ባሕረ ሰላጤው፣ ወደ አረቦች እና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፋፍታለች። በዚህም አሜሪካ የበላይነቷን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች ”- የወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ስለመሆኑ ከጂዮፖለቲካዊ አኳያ ከወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል በአፍሪካ ያለውን የጸጥታ እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃገብነት ጉዳይ ከሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር)የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰር ጋር ቃኝተነዋል። በመጨረሻው ክፍል ከሚያዝያ 8-9 ፣ 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው የአደጋ ስጋት አስተዳደር አቅምን በተመለከተ ከቻርሎት ኖርማን፣ የጋና ብሔራዊ የአደጋ አስተዳደር ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር ጋር ዳሰነዋል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

See all episodes