የሩሲያ 10 ኢምባሲዎችን በአፍሪካ ዳግም የመክፈት እቅዷ ለተጠናከረ ወዳጅነት

March 4
1 hr

Episode Description

''የአፍሪካና የሩሲያ ግንኙነት ዘመን ተሻጋሪ ነው። ሩሲያ ካደጉ ደግሞ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ ሀገራት አንዷ ናት። ለምሳሌ ድምፅን በምድፅ የመሻር አቅሟን ማንሳት ይቻላል። ስለዚህ ከእንዲች ያለች ሀገር ጋር ወዳጅነት መፍጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው - ሩሲያ በቀጣይ ዓመታት ወደ አስር የሚጠጉ ኢምባሲዎችን በአፍሪካ ለመክፈት ማቀዷ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነትን የሚጨምር ነው'' ሲሉ የአፍሪካ ፖሊሲ ጥናት ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው መርሃ ግብራችን በክፍል አንድ ሩሲያ በአፍሪካ አህጉር አስር ኢምባሲዎችን ዳግም ለመክፈት የገለፀችበትን ዕቅዷን መሠረት አድርገን የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ እንዴት የዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ እንደሚያጎለብት እና ዕድሎችን እንዲፈጥሩ እንደሚያስላቸው ከፖሊሲ ጥናት ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። በክፍል ሁለት ደግሞ ስለመረጃ ሉዓላዊነት እና የሠው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር ከኮምፒውተር ሰርቨር ቁጥጥር አስተዳደር ባለሙያው ታደሰ ፀሃይነህ ጋር እንቃኛለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes