Episode Description
ዓለም የባዮሎጂካል ብዝሃነት ዓለም አቀፍ ቀንን በፈረንጆቹ ግንቦት 22 ቀን ያከብራል።
'' አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የተጋለጠች አህጉር ነች፣ በእርግጥ አንድ ዓይንት ስነ ምህዳር አይደለም ያላት። ስለዚህ ይህ የሀገር በቀል እውቀት ለብዝሃ ህይወት ይጠቅማል። ብዝሃ ህይወት ስንል ብዙ ዝርያ ያላቸው እንስሳት፣ ዕፅዋትና ደቂቀ ነፍሳትን አንድ ላይ የያዘ ነው '' - ሲሉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካን ስነ ኑረቶችና ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን ሚናዎች የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ጋር ቆይታን አድርገናል።
በክፍል ሁለት አፍሪካ በዓለም አቀፍ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ዕድገት ጉዞ ያላትን ቦታ ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሰርቨር ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሙያው ታደሰ ፀሃይነህ ጋር ቃኝተነዋል።
ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: