ህጻናትና ወጣቶችን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጫናዎች የመጠበቅ ኃላፊነት

May 4
1 hr

Episode Description

''አሁን ላይ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አስፈሪ በሚባል ደረጃ እየሄደ ያለ ነው። የተለያዩ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው። እነዚህ ልጆችም ለማይሆኑ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ — የዲጂታሉ ዓለም ገደብ የለውም። ከስነልቦና፣ ከእውቀታቸውና ራሳቸውን መቆጣጠር ከሚችሉበት በላይ የሆኑ ነገሮችን እየተመለከቱ ለብዙ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ። ጥፋቱ ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን - '' ሲል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋራው ብሩክ ጫላ ለስፑትኒክ አፍሪካ አፍሪካ ተናግሯል ።

ሶቨርኒቲ ሶርስስ
በዛሬው ዝግጅቱ በክፍል አንድ ታዳጊ አፍሪካውያን ህጻናትን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ካልተፈለጉ ጫናዎች ስለመከላከል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋረው ብሩክ ጫላ ዕይታውን ያጋራናል።

ክፍል ሁለት እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ እና የዓለም ባንክ ባሉ ተቋማት በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ደረጄ መለስ ጋር እንወያያለን።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes