Episode Description
“ካፒታሊዝም [የምዕራቡ] በመሰረታዊነት የተመሰረተው በኢኮኖሚ ብዝበዛ ላይ ነው [...] አሁን የቀድሞ የፈረንሳዪ ቅኝ ግዛቶች «የቅኝ ግዛት መገበያያን» አንጠቀምም ባሉ ጊዜ የነዚህ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እስከ ፖለቲካዊ ግድያዎች ድረስ ገጥሟቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ «የቅኝ ግዛት መገበያያዎች» ለአውሮፓውያኑ የአመት ገቢያቸው ነው፣ የአፍሪካን ገበያ የሚቆጣጠሩበት ነው” ሲሉ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ወደ ቀጠናዊ ሉዓላዊነት ቁርጠኛ ሽግግር እያደረገ ወደሚገኘው የሳህል ቀጠና ይወስደናል። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑትን እንደለ ንጉሴ አውርተናል። ድረም ኦቭ ቼንጅስ በሁለተኛው ጉዳዩ፣ የሀገርበቀል የሰላም ጥረቶች ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊ መፍተሄዎች ከመፍታት አንፃር የሚኖረዉን ትርጉም እንቃኛለን። ለዚህም የፌዴራል ጥናቶች ተመራማሪና የምክክር ሂደቱ ተሳታፊ ኃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር)እና የሐይማኖት መምህር እናየምክክር ሂደቱ ተሳታፊ ቀነዐ ለሚን እንግዳ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: