የመጨረሻው ምሽግ፦ በአገር በቀል ዘሮችና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ በአፍሪካ

July 11
1 hr

Episode Description

“በምዕራባውያን አምሳል የተነደፉ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የአገር በቀል የእህል ዘሮቻችን አዋጭነትን ዝቅ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለባቸው። ነገር ግን እውነታው ዘሮቻችንን ያጣን ዕለት ማንነታችንን የማጣታችን ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት እነዚህ የውጭ ኃይሎችና ግዙፍ ኩባንያዎች ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረውታል። በአፍሪካ እስካሁን እጃቸውን ያላስገቡበት ብቸኛው ዘርፍ ቢኖር ምግባችንና የምግብ ስርዓታችን ብቻ ነበር። አሁን አሁን ይሄንኑ የመጨረሻ ምሽጋችንን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ፍጥነት እየመጡ ነው” ሲሉ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ ባሉ ኃይሎች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንደምን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የዕለት ጉርስ ላይ ስጋት እንደሚሆን እንመረምራለን፤ ይህ ሁኔታም የምግብ ዋስትና በሎም ዋነኛ የብሔራዊ ደህንነት እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የመሆኑንም ነገር ያስቃኘናል። ለዚህም የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ዋና አስተባባሪ የሆኑትን ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) አነጋግረናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

See all episodes