አፍሪካ የቆዳ ማንጫ ቅባቶን የመጠቀም ልማድ ማሻቀብ፣ መንስኤዎቹ እና ማህበራዊ መዘዞቹ

Dec 31, 2025
1 hr

Episode Description

“አፍሪካውያን የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን እንዲጠቀሙ ከሚገፋፉ ምክያቶች መካከል የምዕራቡ ዓለም የውበት መስፈሪያ የራሱን አስተዋፅኦ አድርጓል[…]ምርቶች እንዲሸጡላቸውም በማህበራዊ ሚዲያ የውበት መስፈርትን የሚያወጡ ዓለም አቀፍ ተቋማትም አሉ” ሲሉ በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በመላው አፍሪካ፣ የቆዳ ማንጫ ቅባቶችን የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መማጣቱን በማንሳት ጤና እና አጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለውን ቀውስ እንቃኛለን። በዚህ ወሳኝ ጉዳይ ዙሪያ ሞያዊ ምልከታቸዉን እንዲያጋሩንም በአለርት ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር ሕክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አኒሳ በፈቃዱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ ከ 12,000 ዓመታት በኋላ እንደፈነዳ የተነገረለትን የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የጠፈር ሳይንስ እና የስነ ፈለክ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑትን ፕሮፌሰር አታላይ አየለን አነጋግረናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

See all episodes