በአውሮፓ እስረኛ የሆኑ ቅርሶች፡- ኢትዮጵያ ቅርሶቿን የማስመለስ ትግል

January 29
25 mins

Episode Description

የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ90-95 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ የባህል ቅርሶች ከአህጉሪቱ ውጭ ይገኛሉ። ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ሙዚየሞች ብቻ ከ500,000 በላይ የአፍሪካ ቅርሶችን ይዘዋል።ከእነዚህም አብዝኃኛዎቹ በቅኝ ግዛት ዝርፊያ፣በአስገዳጅ ሁኔታዎች ወይም በሕገ-ወጥ ዝውውር የተገኙ ናቸው።

"ከአገራችን ተዘርፈው ተወሰዱ ቅርሶቻችን በክፍያ መልሰን እንድንወስድ መጠየቃችን አሳዛኝ ነገር ነው። እነዚህን ቅርሶች የያዙ ሙዚየሞች ወይም የግል ቅርስ ሰባሳቢዎች ወደኢትዮጵያ እንዲመልሷቸው እናበረታታለን"ሲሉ የሺ ካሳ፣ የራስ ደስታ ዳምጠው የልጅ ልጅ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አባተ ጎበና (ዶ/ር) በበኩላቸው "በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደኢትዮጵያ የመጡ እንግሊዛውያን፣ አስቀድመው ስለኢትዮጵያ ውድ ቅርሶች ያውቁ ነበር። ቅርሶቹን ለመዝረፍ በጀት ተመድቦላቸው የመጡ ባለሞያዎችም የሀገሪቱ ቅርሶች ዘርፈዋል።[...] ምዕራባዉያን [በማንኛውም መልኩቢመጡ] ባዶ እጃቸውን ግን አይመለሱም ነበር።" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በምእራቡ ዓለም እስረኛ የሆኑ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ቅርሶችን ጉዳይ እንመረምራለን።

እንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

See all episodes